አንተ እግዜሩ አገረ-ኢትዮጵያ ሰው አጥታለችና አንተው ምራት!!
አንተ እግዜሩ አገረ-ኢትዮጵ ያ ሰው አጥታለችና አንተው ምራት!! አንድ የአገራችን ምሁር በኦሮምያ እና አማራ ህዝቦች መካከል የነበረውን እና ስላለው የጠበቀ ዝምድና ሲያወራ አያይዞም ስለሚከሰቱ ግጭቶች ተናግሯል፡፡ “በአማራ እና ኦሮሞ ህዝቦች መካከል ያለው ከመጋባት ፣ ከማስረግ ፣ አብሮ ሃዘን ደስታን ከመካፈል ውጭ ምንም የልዩነት ታሪክ የለንም፡፡ እንደሚባለው እንኳ አለ ብለን ብናስብ የነበረው ፖለቲካዊ ስርዓት እንጅ ህዝቡን የሚመለከት አይደለም፡፡” ይሄነን ሃሳብ የፅሁፌ መነሻ ያደረግሁት አሁን በየአካባቢው የሚከሰቱ ዘርን ያነጣጠሩ ግድያዎችን … እያስተዋልን ባለበት ሰዓት መነሻቸው ምንድነው? ገዳይና ተገዳይ ስለምን እንደሚገዳደሉስ ያውቁታል ወይ? ሟች የሚሞትበትን ሰበብ ያውቀዋል ወይ? ገዳይ የሞት ሰይፍ የሚከነዳበትን ምክንያት ያውቀዋል ወይ? ከ1983 በፊትም ሆነ በኀላ የአገራችን ምሁራን በተለይም ስሙን ማስታወስ ያልቻልሁት አንድ ሰው ታሪካዊ ምክሮችን ለሞተው ጠቅላይ ሚኒስተር አካፍለው ነበር፡፡ የምሁሩ ማህበረሰብ የቻለውን ያክል ራሱን በማግለል ፣ በመተቸት ፣ በመቃወም የስርዓቱ አገር አፍራሽነት ተቃውሟል፡፡ መክሯል ዘክሯል፡፡ የዘር ፖለቲካ ዞሮ ዞሮ የዘር ፖለቲካ ነው፡፡ በአንድ ወቅት የንጉሱ ስርዓት ጎጃምን ጨፍጭፎ ነበር፡፡ ” ሞጣ ቀራኒዮስ ምነው አይታረስ በሬ ሳላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረስ ” ተብሎም ተዘምሯል፡፡ ነገር ግን ቂምም ይሁን የተተከለ ቁርሾ ቅሬታ ጎጃም ውስጥ የለም፡፡ ቢኖር እንኳ የአገሪቱን ንጉሳዊ አስተዳደር ማውገዝ እንጅ የሰራዊቱን ዘር ፣ ማንነት ያጥላላ ወይም ለይቶ የተቃወመ አልነበረም፡፡ የሰዓቱን ፖለቲካ በበላይነት የሚጋልብ የበላይ ዘር ስላልነበረ ንጉሱ ተቆጡ ከማለት ውጭ የተለየ ሆኖ ወደ ማህበረሰቡ ጠልቆ ገብ...