Posts

Showing posts from April, 2021

በአንደኛው ደስታ በሌላኛው ጥርጣሬ ?

Image
በአንደኛው ደስታ በሌላኛው ጥርጣሬ ? ኦቦ ለማ የሚናገሩትን ቃል ልብ ይበሉ፡፡ ልብን የሚነካ ንግግርዎት አፈር ደሚ እንዳይግጥ ከፈለጉ በተግባር ይታጀብልን፡፡ይህ የሚናገሩለት ህዝብ ” የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” ብሎ ከልጁ በላይ ለቃሉ ትልቅ ስፍራ ያለው ነው፡፡                                                                              by; ግርማው አሸብር የዛሬ ምልከታና የግል አመለካከቴን ለማካፈል ሳስብ በጥያቄ ምልክት ጀመርሁት፡፡ ምክንያቱም ሰሞንኛው የኦሮማራ ነገር ሁለት ፊት አድርጎናል፡፡  በአንደኛው ደስታ በሌላኛው ጥርጣሬ ፡፡ የምን ጥርጣሬ ካላችሁ “ያልጠረጠረ ተመነጠረ” ነውና ተረቱ በኀላ ሳንጠረጥር አምነን ፣ የተሰገጸጠንን ሁሉ ሳናኝክ ከዋጥነው መረታትና የሆድ ቁርጠቱም ከባድ ነው፡፡ # ኦቦለማ  የሚናገሩትን ቃል ልብ ይበሉ፡፡ ልብን የሚነካ ንግግርዎት አፈር ደሚ እንዳይግጥ ከፈለጉ በተግባር ይታጀብልን፡፡  ይህ የሚናገሩለት ህዝብ ” የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” ብሎ ከልጁ በላይ ለቃሉ ትልቅ ስፍራ ያለው ነው፡፡ የአገሪቱን ፖለቲካ ለምንም አላማ ይሁን ለምን በኪስዎ ይዘው እንደፈለገዎ እያሾሩት ነው፡፡ እርስዎ ባህር ዳር ከተማ የአማራ ህዝብን በአዳራሽ ሰብስበው ስለኢትዮጵያ ” ለቀባሪ ማርዳት” እንዲሉ ሰብከው አስጨብጭበዋል፡፡  ህዝ...