በርሃብና ኀላቀርነት የምንገረፍበት አለንጋ አንሶን በራሳችን ላይ የዘረኝነት ጅራፍ የምንጨምር ምን ያልታደልን ብንሆን ነው ?
በርሃብና ኀላቀርነት የምንገረፍበት አለንጋ አንሶን በራሳችን ላይ የዘረኝነት ጅራፍ የምንጨምር ምን ያልታደልን ብንሆን ነው ?
…አንዳንዴ ” አህያ አባትህ ማነው ሲባል ፈረስ አጎቴ ነው” አይነት መልስም ያዋጣልና፤ አገርህን ስትጠየቅ ስለቀኝ ግዛት ታነሳና በአድዋ ድል በኩል አድርገህ በአፍሪካ አባት ጃንሆይ በኩል (ራስታ/ራስ ተፈሪ / ጋሽ ቦብ ማርሌይ/ ጃማይካ ብለህ ትቀበጣጥርና በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የሬጌ ቆብ በኩል ዘልቀህ እሱ የፓን አፍሪካ የጥቁር ህዝብ የነጻነት ቀለም ነው ብለህ ለመሹለክ ሞክር፡፡ ያን ጊዜ ምዕት አመታት የእሱን አገር መገዛት እያሰበ ባንተ ነፃነት ሲደመም “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ከርሃብ መርዷዊ ዜናህ ታመልጣለህ፡፡(አልስቅም)
=========================================== ...ይህንንም አስጠላችሁን ፣ አስገደላችሁን ፣ እኛን አትወክሉም ፣ ስማችንን አትጥሩን በሚል አቋም በገሃድ በማንጸባረቅ ህዝባዊነትን መቀላቀል ይቻላል፡፡ ስርዓቱ በወለደው ጉድ ህዝብ ራቁቱን ወጥቶ ሃዘኑን እየገለፀ ፤ ጥቁር ለብሶ አደባባይ በአርምሞ ድምፁን እያሰማ ፣ በየቀኑ ለምን ሰው ተገደለ ሳይሆን ስንት እንደሞተ የሟች ብዛት እየሰማን በምንዉልበት አገር ላይ ምንም እንዳለልተፈጠረ ፀጥ ረጭ ማለት ዠጎረቤት ጎጆ ሲቃጠል እያዩ እንደማላገጥ ይቆጠራል፡፡ ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ነን፡ እንተሳሰብ፡፡ የአንዳችን መጉደል ለሁላችንም ጉድለት ነው፡፡
ከመለስተኛዋ ሱናሜ ምድር አንቀጥቅጥ ሳምንት በሰላም በመመለስና ልብ በማጋባት ዝም ወደማያስብለው የአገሬ ጉዳይ ተመልሻለሁ፡፡ በዚህ ፅሁፌ ውስጥ ግራ መጋባቴን ፣ ውርደት/ ሽንፈቴን ፣ ትዝብትና የአብሮ መኖር ጌጥን ጭምር ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ ስለትግራይ ውስጣዊ ህዝብና ውጫዊ ካድሬዎች ፣ ስለግፉዓን የዘረኝነት ሰለባዎች ፣ እና በተለይም ስለየትግራይ ባላገሮች እና የወያኔ ቁማር እዳስሳለሁ( ሙሉውን እንኳ እንዳትጠብቁ ግን የቀረበውን ብቻ እንካችሁ ፡፡
ከአገር ወጣ ብላችሁ ሰው ስትተዋወቁ ” እንዴት ነህ?” ከሚለው ይልቅ ” WHERE ARE YOU FROM?” ነው መደበኛው ሰላምታ፡፡
ከዚያ ቀጥሎ ነው ትውውቅህ እንደ አገርህ ዝና ወይም እንደአገር ደረጃ የሚሰምረው ወይም የሚከሽፈው፡፡ እኔም እናታለም ለምለሚቷ አገሬ ፣ የጀግና ምድር ፣ ለነጭ ያልተንበረከከ ክንድ ያላት ፣ አረንጓዴዋ ፣ የፍጥረተ ሰብ ምድር ፍኖተ አገር ወዘተርፈርፈ…. የቀጠናው አገራት የጦር ዋና /አንደኛ ፣ ፈጣን እድገት/ውድቀት/ ላይ ያለች::
እና ኮራ ብየ ” አይ አም ፍሮም ኢ ት ዮ ጵ ያ” እንዳልሁ ፊቱ ላይ የአዘን አይሉት የመፀየፍ ነገር ይበተንበታል፡፡ የማያውቃት ሰው ግን የለም፡፡ የማያውቃት ሰው መተዋወቅ እንዴት ደስ ይላል መሰላችሁ፡፡ እንዳለ ሙሉ የጀነት/ገነትን ምድር አድርጌ ስስልለት ሙሉ አድራሻየን ተቀብሎ ፣ እኔን በማዋራቱ ኩራት ተሰምቶት ነው አብሮይ’ የሚቆየው፡፡
አንዳንዱ ደግሞ ስለማያውቃት ልታስረዳው ከሞከርህ ትዝ ትለውና ወዲያው ይለዋወጥብሃል፡፡ ስለዚህ በቃ ብዙ ማብራሪያ አያስፈልግም፡፡ #ዩቶፒያ ብሎ ይለፋት አንተ መተው ነው፡፡
አንዳንዴ ” አህያ አባትህ ማነው ሲባል ፈረስ አጎቴ ነው” አይነት መልስም ያዋጣልና፤ አገርህን ስትጠየቅ ስለቀኝ ግዛት ታነሳና በአድዋ ድል በኩል አድርገህ በአፍሪካ አባት ጃንሆይ በኩል (ራስታ/ራስ ተፈሪ / ጋሽ ቦብ ማርሌይ/ ጃማይካ ብለህ ትቀበጣጥርና በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የሬጌ ቆብ በኩል ዘልቀህ እሱ የፓን አፍሪካ የጥቁር ህዝብ የነጻነት ቀለም ነው ብለህ ለመሹለክ ሞክር፡፡ ያን ጊዜ ምዕት አመታት የእሱን አገር መገዛት እያሰበ ባንተ ነፃነት ሲደመም “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ከርሃብ መርዷዊ ዜናህ ታመልጣለህ፡፡(አልስቅም)
#ርሃብ…. በቃ ከዚህ በላይ ውርደትም ሽንፈትም የለም፡፡ ገና አገሬን ስነግራቸው በዚያን በ77ታችን ስለሰባ ሰባትሺህ ርሃባችን የአገራቸው ዘፋኞች የዘፈኑትን ሙዚቃ ይጋብዝሃል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ሙሉ ሰውነትህን በአይኑ ይፈትሽሃል፡፡ ስለመራብህ ከምትሰማ ቢርብህ ይሻልሃል፡፡ ህመሙ ከባድ ነው፡፡ ከወያኔ አጋዚ የሰደፍ ብትር በላይ ያንጀባርራል፡፡
የሚገርመው በዚህ አመት ከኢትዮጵያ የመጣ አንድ ጓደኛየ የሆነ ጉባኤ ልንሳተፍ አብረን ሄደን ምሳ ላይ ትንሽ ምግብ አነሳ፡፡ ምነው እሷን ብቻ አትበላም እንዴ ስለው ” ባክህ ርሃብተኛ አለመሆናችንን ይወቁ ብየ ነው፡፡” አለኝ( ያው ስቄም በመሳቀቁ ተሳቅቄም አለፍሁት)፡፡ እና አገራችን ስሟ እስከዚህ ድረስ ነው፡፡
(አማርኛችን ባይኖር ኖሮ በእንግሊዝኛ ይህንን የሞራልም በሉት የታራካችን ጥቁር ጠባሳ አልፅፈውም ነበር፡፡ አማርኛ ኑሪ ለውስጥ ጉዳያችን)
ወቅታዊ ጉዳያችንና ላያችን ላይ በአለም የተፃፈው የድህነት ብቻ ሳይሆን የርሃብ ታራካችን እስካሁን ድረስ ቢብስ እንጅ ሳንለወጥ አለን፡፡ ከፊል ኖሯችን ከግንባታ፡ ከምሁራን(በየዩኒቨርሲቲዎቻችን የተሞሰጉ ፎርጅድ ፕሮፌሰር የህንድና የፊሊፒንስ መምህራንን ልብ ይበሉ) እስከ የእለት ጉርሳችን ድረስ በለጋሽ አገራት በጎነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
የመገናኛ ተቋማችን የምረቃ ፣ የመሰረት ድንጋይ ዜናወች በስተጀርባ ከሆነ አገር በተገኘ የብድርና የርዳታ ድጋፍ በተገኘ ገንዘብ የሚል የኩራት ሚመስል የውርደት አዋጅ አለበት፡፡
#እና_እውን_መላው_ኢትዮጵያ_ህዝብ_ይሄነን_ጉዳይ_ተገንዝቦ_ለውጥ_እኩል_ተነስቷል_ወይ?
ለውጡስ ከየት ነው የሚጀምረው?
ከስርዓት ለውጥ ወይስ ከግለሰባዊ ንቃተ ህሊና?
የትግራይ ነፃ አውጪ ነን ባይ ወያኔ/ህውሃቶች እንኳን ህዝባቸውን ነፃ ሊያወጡ ከአገሪቱ ደሃው ክልል ትግራይ ነው እያሉን ነው፡፡ አዲሱ የወያኔ ሊቀ ወንበር ዶ/ር ገ.ፂ አማረልኝ ብለው በክፉ ቀናቸው ወ/ሮ ፋናየ ቲቪ ብቅ ብለው “ትግራይ ደሃ ናት” አሉ፡፡ በመቀሌ ከሚገኘው አይነት ሙስና ሰፈር ድርብርብ ህንፃ ውጭ ፣ ራሳቸው ካድሬዎች አንዴ ጥረት ሌላ ጊዜ ምናምንቴ እያሉ ከሚያጋብሱት ውጭ የትግራይ ህዝብ በድህነት አረንቋ የሚሰቃይ ስለመሆኑ የዩኒቨርስቲ ጓደኞቼ የተማሪነት ህይወት ምስክር ነው፡፡
እውነት ነው ትግራይ አሁንም ድረስ እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ጭቁኑ አርሶ አደር ከወያኔ የተረፈው ነገር የለም፡፡ የተረፈው ቢኖር ጥላቻን፡ ጦርነትን ብቻ ነው፡፡ ከራሳቸው የወጡ የደደቢት ሽፍቶች አፍነው አላናግራቸው ቢሉ እንጅ በኔ ትዝብት ወያኔን/ የአገሪቱን አምባገነን ስርዓት አምርሮ በአደባባይ መታገል የነበረበት የትግራይ ህዝብ ነው፡፡
በክልሉ ውስጥ ከአምስት በላይ ብሔረሰብ ይኖራል፡፡ አሁን ስለመኖራቸው አጠራጣሪ ነው፡፡ ምክንያቱም በምንም አጋጣሚ በክልሉ ቴሌቪዥንም ይሁን በህውሃት ተወካዮች ውክጥ እነዚህን ነገዶች የሚወክል አንዳችም ምልክት ታይቶ አይታወቅም፡፡ በስም ጥቀስ ብባል ኩናማን ብቻ በሙዚቃ አውቀዋለሁ(በሙዚቃ ብቻ):: ግን የትግራይ ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡
አዜብ ደሃ ነኝ ባለች በሳምንቱ ከጨዋታ ውጭ ከፈታትረው ከጨዋታ ውጪ ያደረጓት እነዶ/ር ገ.ፂ አሁንም የትግራይን ህዝብ እንኳን ነፃ ሊያወጡ(ከምን ነፃ እንደሚያደርጉት ባላውቅም) በአንፃሩ ከኢትዮጵያዊያን ፍቅር ነፃ ፣ ከኢትዮጵያዊያን አንጀት ነፃ ፣ ከኦሮምያና አምሃራ ወንድሞቻቸው ፍቅር ነፃ እያደረጓቸው ያሁነያ፡፡ ከአብሮ መኖር ባህል ነጻ ፣ ከጨዋነት ትውፊት ነፃ ፣ ከትህትናና መቻቻል ነፃ እያደረጓቸው ያሁነያ፡፡
እና የትግራይ ህዝብ ድሮም ነፃ የነበረ በማንኛውም የአገሪቱ ክፍሎች በፍቅር ፣ በመተሳሰብ የኖረ ፣ ተዋልዶና ተጋብቶ ለረጅም ዘመናት ኖሯል፡፡ አሁን ግን በወያኔ በመጣ ሰበብ ከኢትዮጵያዊያን ጋር አብረው የኖሩበት የአንድነት ፣ የአብሮመኖር ሰንሰለት ሊበጠስ አንድ ሃሙስ የቀረው ይመስላል/ተበጥሷል የሚሉም አሉ፡፡
በተፈጥሮው በቂ ሰብል አብቅሎ መመገብ የማይችል ቀየ ላይ የሚኖር ህዝብ ኑሮው ከአገሪቱ ጋር ባለው ህዝብ ለህዝብ ትስስር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንን የሚያውቅ ህዝብ ግን በአጭር ጊዜያት ውስጥ በመላው አገሪቱ(ማህበራዊ ሜዲያ ጭምር) ትግሬ የተባለ ከወያኔ በላይ የድርጅቱ ቂም መወጫ ሲሆን ከአገሪቱ ህዝቦች የአንድነት ሃሳብ ጋር ወግኖ ዘላቂ አብሮነትን እንደማጠናከር የድርጅቱ ልሳን ለመሆን መሞከር የበለጠ ጥላቻውን ያገነነው ያህል ታዝቤያለሁ፡፡ እና ዞሮ ዞሮ አሁንም ጊዜው አልረፈደምና ህዝብና ፓርቲን በመለየት ውግንናው ለራስ(ለአገራዊ አብሮነት) ማድላት ቢሆን መልካም ነው፡፡
ለስራ ጉዳይ በ2008 ዓም ወደትግራይ የመጓዝ እድሉ ነበረኝ፡፡ በአይኔ የተመለከትሁት ከማይጨው በረሃ ጀምሮ መቀሌ እስክገባ እንኳን ምድሩ ቤቶቹ ድንጋይ ካብ ቀመስ ናቸው፡፡ ጭው ያለ በረሃማ ፀሃይ ነው የሚስተዋለው፡፡ አልፎ አልፎ አፈር ለብሰው ያንን ኮረንኮች ድንጋይ የሚያርሱ ምስኪን አርሶ አደሶች ተመልክቻለሁ፡፡ ምናልባት ለአካባቢው እንግዳ ስለነበርሁ ለአይኔም እንግዳ ሆኖብኝ በትምህርት የማውቀውን የማይጨው አስደማሚ ሰንሰለታማ ተራራ እየተመለከትሁ አካባቢውን ከጦር ሜዳነት ውጭ ለሌላ የተመቸ ነው ብዩ አላሰብሁም( ማይጨው ተራራን)፡፡
በመሆኑም የትግራይ ህዝብ በሃይማኖቱና ሃበሻዊ ውብ ባህሉ የእውነት የኢትዮጵያዊነት ማንነት የሚስተዋልበት እንግዳ አክባሪና ከአንደበቱ በሚወጣው ንግግር ሁሉ በፍቅር የሚጥል ሆኖ ታዝቤዋለሁ(እያወራሁ ያለሁት እዛው ስለሚኖረው ባለሃገሩ ትግሬ ነው) ፡፡ እኔ የማውቀው ታዲያ ከክልሉ ውጭ በዩኒቨርስቲ ቆይታዩ ፣ በሌሎች ከተሞች በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ ፣ በአማራ እና ኦሮሞ ህዝቦች ጋር የሚኖሩትን ከዚያም ሲያልፍ በክድርና ዘመቻ ላይ ያሉትን ነው፡፡
እዚህ ጋ ትዝብት፡ –
በዩኒቨርስቲዎች ሁሉም ተወላጆች የወያኔ ህውሃት መሰረታዊ አደረጃጀት እስከ ካንፓስ ኮሚቴ ፣ ህዋስ አመራር በየ ትምህርት ክፍሉ ፣ በተማሪ ህብረትና የሰላም ፎረም ላይ ሰፊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ በከተሞች የከተማ ትግራይ ተወላጆች ማህበር በማቋቋም ከማህበራዊ ህይወት ትስስር (ይሄ ቆንጆ ሆኖ)ባለፈ በአደረጃገ፡ጀቱ ውስጥ የስለላና ደህንነት ስራን ይሰራሉ፡፡ (በሁሉም ክልሎች)
ጥያቄ :-
ስለምን ህዝብ ሆነው መኖር አልመረጡም?
ህዝቡስ ስለምን ጠላን /ይሸሸናል ብለው ማሰብ አልቻሉም?
ማጠቃለያና ስጋቴ፡-
ኢትዮጵያዊነት አብሮነት ነው፡፡ የአብሮ ሐኖር ውጤት ነው፡፡ ቀድሞ የነቃው አገርን እየጠበቀና ከጠላት እየተከላከለ በኀላቀርነት ኑርዘዴ የተተበተቡ አገረኛ ህዝቦችን የማንቃትና የማሰልጠን ተደጋግፎታዊ ኢትዮጵያዊነትን አብረን ኖረነዋል፡፡ ከውርስ የተቀበልነውም ይህንኑ ነው፡፡ በመሆኑም ህዝብ ብዙ ነው፡፡ አንድ ነገድ ደግሞ ውስን ነው፡፡ የአገራው ህዝብ የለውጥ እንቅስቃሴ አይመለከተኝም በማለት እንደውም የለውጥ እንቅስቃሴው ላይ እንከን ለመሆን በተደረገ ሙከራ ለውጥ አቢዮት ላይ ነኝ የሚለውን ሰፊ ህዝብ ያስቆጣ ነው፡፡ አቢዮት ደግሞ ገንፍሎ ሲወጣ ሰደድ እሳት ነው፡፡ ያገኘውን ያቃጥላል፡፡ እናም ህዝብ መሆን የተሻለ ይመስለኛል፡፡
ይህንንም አስጠላችሁን ፣ አስገደላችሁን ፣ እኛን አትወክሉም ፣ ስማችንን አትጥሩን በሚል አቋም በገሃድ በማንጸባረቅ ህዝባዊነትን መቀላቀል ይቻላል፡፡ ስርዓቱ በወለደው ጉድ ህዝብ ራቁቱን ወጥቶ ሃዘኑን እየገለፀ ፤ ጥቁር ለብሶ አደባባይ በአርምሞ ድምፁን እያሰማ ፣ በየቀኑ ለምን ሰው ተገደለ ሳይሆን ስንት እንደሞተ የሟች ብዛት እየሰማን በምንዉልበት አገር ላይ ምንም እንዳለልተፈጠረ ፀጥ ረጭ ማለት ዠጎረቤት ጎጆ ሲቃጠል እያዩ እንደማላገጥ ይቆጠራል፡፡ ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ነን፡ እንተሳሰብ፡፡ የአንዳችን መጉደል ለሁላችንም ጉድለት ነው፡፡
ሰው ሞተ ሲባል የትኛው ብሄር ተገደለ የሚል የራስ ብሔር ሲሆን ያዙኝ ልቀቁኝ ፣ የሌላ ሲሆን የሰላም እንቅልፍ ማጣጣም ከሰብዓዊነት መነጠል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት አይደለም፡፡
እናም ይህንን ሁሉ የምለው ኤርትራን ፣ ጅቡቲን ሶማልያን ተነጥቀን ከሰፊነታችን ወደ ጥቂትነት መገጥተን ከመጠናችን ወርደናል፡፡ አሁንም የመገነጣጠል ህገመንግስትን እኔ ከመወለዴ በፊት አርቅቆ አገርን የተቆጣጠረ ቡድን “ተው/አይሆንም” መባል አለበት፡፡
አንደኛውን ጅምላ ጭፍጨፋ ሌላኛውን የሞት አደጋ ብንለውም ፣ አንዱን የአካል ጉዳት አንዱን የሰው ህይወት ማለፍ እያልን ስመሙን ብንለውጠው ፣ ከትግሬ ወገን ፣ ከኦሮሞ አልያም ከአማራው በኩል እያልን ብናዘበራርቀው ሁሉም ሟችም ይሀሁን ገዳይ ኢትዮጵያዊያን ነን፡፡ አንዳችን ለአንዳችን ጥፋት መሆን ዛሬ ያብቃ እና ለብዙሃኑ የለውጥ ድምጽ አብረን ነጋሪቱን በጋራ ብንጎስመው ስደተኛውም ፣ ህመምተኛውም ፣ ተጨቋኝ ዝምተኛውም ፣ የሚርመጠመጠውም ያ የጋራ ድምጽ የማሰባሰብ ሃይል አለው፡፡
አገራችን በሪፖርት እንደሚቀርበው አይደለችም ወይም ቻይና እንደሚገነባው ህንፃ አይደለችም፡፡
ሃገራችን መልኳ በርሃብና በርዛት ፣ በጭቆናና ኀላቀርነት የተተበተበች ናት፡፡ እና የማናፍርባት አገር እንድትኖረን በመጀመሪያ ከዚህ ዘግናኝ ማንነት ለመውጣት በጋራ እንታገል የምትል ውስጠ ወይራ ሃሳብ አለችኝ፡፡ አብረን ስለሌሎቻችን እንኑር!!
#በርሃብና_ኀላቀርነት_የምንገረፍበት_አለንጋ_አንሶን_በራሳችን_ላይ_የዘረኝነት_ጅራፍ_የምንጨምር_ምን_ያልታደልን_ብንሆን_ነው?
Comments
Post a Comment