ኦሮሞና አማራ ከኦህዴድና ብአዴን በጋራ ድምረት በሚል የግል አስተያትና ትዝብት ፣ መላምትና ስጋትን ለማካፈል ፅሁፉ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የኦሮማራ ፈተናዎችና መፍትሄዎች ምን አንደሆኑ ለመቃኘት ይሞክራል፡፡ ብአዴን ከኦህዴድ በምን ፍጥነት እየተራመደ እንደሆነም ይነካካል፡፡ የኦህዴድ ሞተር ሆኖ የተገጠመለት የኦሮሞ ህዝብ ከሆነ የብአዴን ህዝባዊነትን በተግባር መዋሃድ ላይ ምን ውስንነቶችና ችግሮች ለማየት ይሞከራል፡፡ በመላምትነት የመደመር የዶ/ር አብይ ፖለቲካ ኦሮ-ማራ ሲደመር ኦህ-አህዴን ስሌት ምን ያህል ነው?
ኦሮማራ የተከበረ እና የነበረውን የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን አጠናክሮ የጣልቃገብ ጥላቻ ፖለቲካውን ድንበር ጥሶ መሻገር ችሏል፡፡ በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ የደሴና ነቀምት የእግርኳስ ጨዋታ የባለሜዳዎች አቀባበልና መስተንግዶ ፣ የጣናኬኛ ዘማቾችና የጎጃሜዎች የደብረማርቆሱ ፣ የፍኖተሰላም ፣ የኢንጅባራው አቀባበል ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጋራ የተቃውሞ ተመሳሳይ ድምፆች ፣ የፋሲል ከነማና አዳማ ከነማ ጨዋታ የናዝሬቶቹ አቀባበል በፍቅር የተለወሰ ፣ የዘላለም አብሮ መኖር ስንቅ የሆነ ነው፡፡
ጎንደር ላይ የኦሮሞው ህመም የሚጠዘጥዘው አማራ ፣ አዳማ ላይ የአማራው መጨፍጨፍ የሚያመው ኦሮሞ ለዚህም ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያሰማ ኦሮማራ ተገንብቷል፡፡ ይሄ ጭንቅና ችግር ድንገት ዛሬ የወለደው ሳይሆን ከአፄዎቹ ጀምሮ ከሃረርጌ፣ ከሸዋና ወለጋ ጎጃም ድረስ ፣ በወሎ ከሚሴና ከረዩን አጠቃሎ በደምና በስጋ የተሳሰረ ፣ የአድዋ የነፃነት መስዋዕትነት ከፍሎ ያገኘውን ድል በጋራ ያጣጣመ ትውልድ ስለሆነ ነው፡፡ የአሁኑ እንደ አዲስ የመገለጡ ነገር የጥላቻ ሃውልትን በመካከላቸው እየገነባ ሲያበላላ የነበረው ” ጠባብና ትምክህተኛ” የሚል ለምድ ደርቦ የአናሳ አስተሳሰብ ፖለቲካን ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሲያራምድ የቆየው የወያኔ የግፍ አገዛዝ ነው፡፡ መታሰሩ የበዛበት ኦሮሞ ፣ መፈናቀልና መገደሉ የፀናበት አማራ ዛሬ እንደ ህዝብ የአንድነት ድምፁ ሰማይን የሚያፈካ ሆኖ እየደመቀ ነው፡፡
ከማዕከላዊ ሁለት አመት ካለ ፍርድ በድብደባ ላይ ቆይቶ የወጣ አንድ የኦሮሞ ልጅ “የኦሮምኛ ቋንቋ ቃሊቲ ውስጥ መርማሪ ትግሬዎች ሁሉ ለምደዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ስቃየኞች ኦሮሞ በመሆናቸው ኦሮሞ በስቃዩ ውስጥ ስሜቱን የሚገልፀው በኦሮምኛ በመሆኑ ሁሉም ገራፊ ትግሬዎች ኦሮምኛ ለምደዋል ” ሲል ፅፎ አንብቤያለሁ፡፡ አሁን የጅምላ ግድያው እና እልቂቱ በጎንደር ፣ በባህርዳር ፣ በአምቦ ፣ በጨለንቆ ፣ በወለጋ ፣ በቢሾፍቱ ከተጀመረ አመታት አልፈውታል፡፡ አሁንም አልቆመም ባሰበት እንጅ፡፡ ይህንን ለመመከት የሚያስችል ቄሮ የተባለው ህዝባዊ ሃይል ባንቀሳቀሰው አቢዮት የኦሮሞን ችግር ሰምቶ ከወያኔ ጋር ለመፋለም የሚችል ኦህዴድን ጠፍጥፎ መስራት ችሏል፡፡ ኦሮምያ ውስጥ ህዝብና መንግስት እከከኝ ልከክህ መባባል ከጀመሩበት እለት ጀምሮ ጠላትና ነገረ ሰሪው ማን እንደሆነ ፣ በክልሉ ውስጥ ምንም አይነት ችግር ፈጣሪ እንደሌለ አረጋግጠው ለማ ኬኛ ፣ አብይ ኬኛ ፣ ዳውን ዳውን ወያኔ ድምፅን አንግሰዋል፡፡ የመሪዎቻቸው ደጀን ሆነዋል፡፡ ጀግና ፈጥረዋል፡፡
ዶ/ር አብይ አህመድን ከሚኒስተርነት ወደ ክልላዊ መሪነት ወስደው ሾመዋል፡፡ ባገኙበት አጋጣሚ ሁሉ ይስሙታል፡፡ በአገራችን ታሪክ ሰው መግደል ዋናው ስራው ያደረገውን የወያኔ ታጣቂ ለህግ ማቅረብና ማሰር ጀመሩ፡፡ ህገወጥ የወያኔ ሌቦችን መማረክ ፣ ማዋረድ ፣ መፋረድ ጀመሩ፡፡ ድብቅ ሴራ ይዘው አድማና አመጽ የሚጠሩ የወያኔ ሰላዮችና የትግራይ ተወላጆች እሰስከ ሚጠቀሙበት ፈንጅ ቦንብና ሽጉጥ ፣ ጠመንጃ ድረስ ተይዘዋል፡፡ ተጨማሪ ማሳያም ጫት ፣ ከሰል ፣ ስኳር በህገወጥ የሚያዘዋውሩ የወያኔ የመከላከያና የፀጥታ አገልግሎት ተሽከርካሪዎችን ማርከዋል፡፡ ብዙ ብዙ ብዙ….
የኦሮምያ ልጆች ድሮ እየሞቱ ስቃይን ከሚጠጡበት ዘመን ይልቅ ዛሬ እየሞቱ የሚያስመዘግቡት ተጋድሎ ህጋዊ ፣ አግባብና ሰብዓዊ ከመሆኑ ባሻገር በሃገር አፍቃርያን ዘንድም ለኢትዮጵያ ትልቅ ፈውስ ሆኖ እየተቆጠረ ነው፡፡ ትልቅ አድናቆትና ድጋፍንም ተችሮታል፡፡ አማራ አሁንም እየሞተ ነው፡፡ ከብዓዴን ውስጥ ከሁለት የማይበልጡ ሰዎች ህዝባዊ ናቸው፡፡ እነዚህን አምኖ ድጋፍ ለመስጠት የእምነት ድፍረት ያገኘ አይመስልም፡፡ የህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አባላት እንኳ “ስሜ አይጠቀስ” እያሉ ነው ሃሳብ ለሚዲያ የሚገልፁ፡፡ ሰቆቃው በህዝቡ ብቻ ሳየይሆን እዛው ከውስጣቸው ባለሉ ሹማምንቶች ድረስ የዘለቀ ነው፡፡
አማራ ኦሮሞን ሲበላ የኖረ ለማስመሰል የተሰራው የወያኔ ሴራ በባህርዳሩ የርስበርስ ግንኙነት የተሰበረ ቢሆንም ብአዴን ኦህዴድን መሆን የከበደው ይመስላል፡፡ በዚህ ሰዓት አማራ ማንም ወገን ነፃነቱን እንዲያስከብርለት ፣ ደህንነቱ እንዲረጋገጥለት ብቻ ነው የሚፈልገው፡፡ ስለዚህ ብዓዴን በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከህዝቡ ጋር የእምነት መስተጋብር መፈፀም አለበት፡፡ ያሉበትን ከባድ ፈተናዎች ለህዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ከብዓዴን ካቢኔ ውስጥ ያሉ የወያኔ እትብት የታሰረላቸው አማርኛ ተናጋሪ የትግራይ ነፃ አውጭዎች ደጋፊ ለቃቅሞ ማባረር አለበት፡፡ አቶ ደመቀ መስራት ካቆመ እንደገና Install ሊደረግ ይገባዋል፡፡ ይህ ሆኖ ካልተቻለ ብአዴን አሁንም ከአናቱ ላይ ያሉ አካላት ልጓሙን የያዙበት ነው የሚመስለው፡፡
የኦህዴድ ፖለቲካ አባዱላን ተጠቅሞታል፡፡ አባዱላ ለቀቅሁ ባለ በነጋታው የኦሮምያ ወጣቶች ጀግና ብለው የፌስቡክ የገፃቸው ምስል ምልክታቸው አድርገውታል፡፡ ህዝብን ለማንኛውም ዘመቻ ማሰማራት የሚችል የህዝብ ሃብት አፍርቷል፡፡ ዲሞክርሲያዊ አሰራርን ማዕከላዊ አድርጎ ህዝባዊ መንግስት ለማቋቋም ዳዴ ላይ ነው፡፡ አሁን የውስጥ ጉዳይ የለበትም፡፡ ከውጭ በወያኔ አሸባሪ ከተባሉ ፖለቲከኞች ጀምሮ እስከ ውስጣዊ ወጣቶች ድረስ አፍ ማስያዝ የሚያስችሉ ለውጦችን አሳይቷል፡፡ አሁን ለህዝቡም ይሁን ለኦህዴድ ፈተናው ወያኔ ብቻ ስለመሆኑ መግባባት ላይ ደርሷል፡፡ በፈጠረው አቅሙ ሳይፈልግ ሲፈጠሩለት የነበሩ የወያኔ ተንኮል አጀንዳዎችን ውድቅ ማድረግ ፣ የአገሪቱን ምክርቤት ስብሰባ እስከመበተን ሞገድ አግኝቷል፡፡
ብአዴን በትንሽ ቁጥር ያላቸው አካሎች መንቃት ላይ ነው፡፡ ዶክተር አምባቸው ፣ አቶ ገዱ ፣ ዝምተኛው አቶ ብናልፍ እናንተ ብቻ ማርሹን መቀየርና ብረቱን የአማራ ህዝብ ደጀን አድርጋችሁ የታሰራችሁበትን ቀንበር መበጠስ ትችላላችሁ፡፡ ጎጃም ፣ ጎንደር ፣ ሸዋ? ፣ ወሎ በድፍረት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲዋደቅ የነበረው ከውጭ ስላለው ጣልቃ ገብ ጭቆና የተነሳ ነው፡፡ የበላይነቱ ይብቃ ፣ የኢኮኖሚ እና የወታደራዊ ሃይል የበላይነቱ እስከመቼ? ብሏል፡፡
ከደደቢት እስከ አራት ኪሎ ከሰላሳ አመታት በላይ አምባገነንነትን እየኮተኮቱ ለዚህ መከራ ያበቁት የአማራ ተወካይ ነን ባዮች በ1983 ዓ/ም የጎጃም ፣ ጎንደር ፣ ሸዋንና የወሎን ምድር ያለምንም ተቃውሞ እጃቸውን ጎትተው አሻግረው ቤተመንግስት የያደረሷቸው አማራን ወክለናል ባዮች (ከንቱው ታምራትን ጨምሮ ፣ በረከት ፣ አዲሱ ፣ ካሳ ፣ተፈራ ዋልዋ ፣…) አሁን የት ናቸው? እሳት ዳር ጥደዋችሁ Silent mood ላይ ናቸው፡፡ እናም ህዝብ ለመምራት ከህዝብ ጋር መዋል ማደር ያስፈልጋል፡፡ እንጋባ ባይ ነው የአማራ ለውጥ ናፋቂው ህዝብ!! ብአዴን ዛሬ አርሶ አደሩ ድረስ ገብቶ ስለራሱ ምክረ ሃሳብ ቢጠይቅ እስከ አፍንጫው ማንነቱን ይነግሩታል፡፡
ምን ያድርጉ?
አሸባሪ ፣ ፅንፈኛ ፣ ነፍጠኛ ፣ ትምክተኛ እየተባለ ለስደት የበቃው ፣ የመናገሪያ ሞራሉን ስለልጆቼ ስለጎጆየ ብሎ አንገቱን የደፋው ፣ የአኮረፉ ምሁራን ፣ በአምባሳደርነት ሰበብ ከአገር የተባረሩ የህዝብ ሰዎች(እንደ አያሌው ጎበዜ አይነቶችን) ፣ ዲያስፖራ ስለአገሬ ይመለከተኛል ባዮችን ፣ በግፍ ስለአገር ፍትህ የታሰሩ ግፋዓንን …ጥሪ በማድረግ ፣ ስለሞራላቸውም ይቅርታ በመጠየቅ ምን እናድርግ? በማለት ውስጣዊ አንድነቱን ማፈርጠም አለበት፡፡
በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ተቋማት ሰጭ እንጂ ተቀባይ ስለላልሆኑ ጥሬ እቃ አስገብተው የሚያመርቱ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ በክልሉ ውስጥ ያሉ ችፑድ ፣ እና ዱቄት ፋብሪካዎች አውዳሚ እንጅ አትራፊ ስላልሆኑ ሊታሰብባቸው ይገባል፡፡ በሰላሳ እድሜያችን ውስጥ ምን አስገኘን? የሚለውን ጥቅል ግምገማ በማካሄድ ከልብ ራስ የመፈተሽ ስራ ያስፈልጋል፡፡ በሰላሳ አመት አንዲት አገር መመስረት ይቻላል፡፡
፩. አማራ ክልል ላይ የተሰሩ የባቡር ፣ የአስፓልት ፣ ገበሬውን ተጠቃሚና አዝማኝ ያደረጉ ምን ቴክኖሎጂዎችን አምጥተናል?
፪. የአማራ ህዝብ ባህል ማዕከል አለው ወይ? የት?
፫. ባህልና ማንነቱ በወጉና በሰብዓዊ ክብር ተከብሮለታል ወይ? የተፈጥሮ ሃብቶቹና የገበሬው ምርትስ ለክልሉ ህዝብ ሲሳይ ሆኗል
ወይ?
፬. የክልሉ ምሁራን የባለሙያዎች ማህበራት አለ ወይ? ምንም!!
፭. በክልሉ ውስጥ ለምልክት ምን ያህል ተፎካካሪ ፖለቲካዊ
ድርጅት አለ? ምንም!!
፮. ከክልሉ ውጭ ያሉ አማራዎች የዜግነት ክብራችው አማራን እንደሚወክል ስልጣን ላይ ያለ ድርጅት ምን ያህል ቁሞላቸዋል?
ወይም ቆሞባቸዋል¡?
፯. በክልሉ ውስጥ ካለ ስለሌትና ጥናት የተሸነሸኑ መሬት ይዞታዎችና የገበሬው አያያዝ ላይ ያለው ህጋዊነትና ዲሞክራሲያዊነት ምን
ያህል ነው?
፰. በጎጃም የመተከል ፣ በጎንደር ሁመራ ፣ መተማ ፣ ወልቃይት ፣ጠገዴ ፣ ግጨው አጎራባች ፣ በወሎ ራያ ፣ አላማጣ ያሉ የአማራ
ህዝብ የውርስ ባድማና ማሳ መሬቱ ተቀምቶ ከውስጥ ከብዓዴን ከውጭ ከሱዳን ፣ ከጎረቤት ከወያኔ ጋር እየተዋጋ ነው ያለው፡፡ አስቸኳይ አቋም መያዝ ያለበት የማንነት ጥያቄ በመሆኑ ህዝብ ያቆየውን ማንነቱን ዛሬ መነጠቅ ስለሌለበት ብአዴን በይፋ አቋሙን ማሳወቅ አለበት፡፡
፱. አማርኛ ቋንቋ ባለቤትህ እኔ ነኝ ተብሎ በ12ኛ ክፍል ፈተና የተገለለው ፣ የምርምርና የመማርያ ቋንቋነት ውጭ የሆነው ፣
በሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ክፍለ ጊዜ በወያኔ ስመ ስነዜጋ ትምህርት አይነት መታጠፉ ሁሉ የጠያቂ ማጣት ጦስ የወለደው ነው፡፡
፲. ክልሉ ውስጥ ያሉ እንደ ዳሽን ቢራ እና መሰል ትርፋማ ተቋማት ለህዝቡ ሲሰሩ ማየት የናፈቀው ትውልድ በጠላትነት
ፈርጇቸዋልና አቀራርቦ በተግባር መታረቅ ያስፈልጋል፡፡
በሚሉና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ላይ መነጋገር ፣ መምከር ፣ የልብ ቃል መግባትና ባለሙያ ወጣት ምሁራንን አሳትፎ አዲስ አቢዮት በመክፈት ለሌሎች የአገሪቱ ወገኖች መልካም ተፅኖ የሚያሳርፍ አስቸኳይ ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህና ሌሎች መሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በጋራ መስራት ካለልተቻለ በቀጣይ ጊዜያትም ብአዴንና አማራ ልክ እንደ ኦሮማራና ወያኔ አጥፊና ጠፊ ሆነው ይቀጥላሉ የሚል የማያጠራጥር ስጋት አድሮብኛል፡፡
=============የተስፋ ዳመና ለኢትዮጵያ!=================
Comments
Post a Comment