Posts

አማርኛ ቋንቋና ኢትዮጵያ

Image
  አማርኛ ቋንቋና ኢትዮጵያ FEBRUARY 9, 2018  /  ግርማው አሸብር (የማዕበሉ ውጤት)   /  EDIT በየትኛውም ቋንቋ የትኛውንም የግል ሃሳብና አመለካከት ማንፀባረቅ ፤ ለምንም አላማ መጠቀም መቻል የአማርኛ ቋንቋ ባህሪ ብቻ ሳይሆን የቋንቋ ተፈጥሮ ነው፡፡ ከአራት አመታት በፊት ደቡብ ክልል አማርኛ እንደሁለተኛ ቋንቋ ሳስተምር ቋንቋውን መናገርና መግባባት የሚችሉት ተማሪዎች ያላቸው በራስ የመተማመን ስሜትና ደስታ በጣም ትልቅ ነው፡፡ ባደረግሁት የዳሰሳ ጥናትም ምክንያቱ የአገሪቱን የስልጣኔ ቋንቋ መናገር በመቻላቸው እና ከከተማ የመጣ ሰው ጋር መግባባት በመቻላቸው እንደሆነ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ፡፡ ያው እንግሊዘኛ የሚፈጥረው አይነት ስሜት፡፡ ነገር ግን ከወደ ትልልቅና በእድሜ ከፍ ያሉ በተለይም ከወረዳ አመራርና ምናምን ጀምሮ ፣ አንዳንድ አካባቢም ዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ቋንቋውን የማጥላላት ነገር አለ፡፡ ይሔ በጥቅሉ የተሳሳተ ግንዛቤና የወቅቱ የሽቀላ ፖለቲካ የሰራው መርዝ ነው፡፡ በዚህ የማህበረሰብ ክፍል ላይ ጥናት ባይደረግም የነፍጠኛ ቋንቋ እየተባለ በደፈናው ጭፍን ጥላቻ ተነዝቶበታል፡፡ ህፃናት በአፍ መፍቻቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዲማሩ የካናዳ ፣ አሜሪካ ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎቹም አገራት በ1960ዎቹ አካባቢዎችና ቀደም ብሎም ጀምረው ለጊዜው መንገራገጮች ገጥሞት የነበረ ቢሆንም በምርምሮችና ማስታረቂያ ፖሊሲዎች በመቅረጽ ስኬታማ መሆናቸውን የቋንቋና ማህበረሰብ ተመራማሪዎች (sociolingust) የጥናት ውጤት ያሳያል፡፡ እንደኛ አገር ህፃናትን በአፍ መፍቻቸው አካባቢያቸውን እንዲያውቁ/ጠንካራ ግንዛቤ እንደኖራቸው በሚል ጠቃሚ መሰረት የተጀመረው የትምህርት ፖሊሲ አተገባበሩ ዘረኝነትን መሰረት አድርጎ በ...

የአድዋ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ(የስራ) ቋንቋ??? ምርቃቷ ርዕስ፡ የእንግሊዘኛ መወፈሪያ የአድዋ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ…

Image
ግርማው አሸብር (የማዕበሉ ውጤት) by :  Girmaw Ashebir ታዲያ ምን ለማለት ፈልጌ ነው …የአድዋ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የነፃነት ድል ከተቀናጀንበት አድዋ ላይ በምን ቋንቋ ነው ትምህርት የሚሰጠው፤ምርምር የሚሰራው? ይህ ጥያቄ ሊታሰብበት የሚገባ ነው፡፡ ዙሮ ለሌላ ማደር ይሉት ነገር እንዳይሆን ስጋቱ የጋራ ይሆን ዘንድ ሃሳቤ ይሔው፡፡ ለዚህች አጭሬ ፅሁፌ መነሻ አንድ የፌስቡክ(የፊትገፅ) ላይ ያየሁትን ትዝብት መነሻ በማድረግ ነው፡፡ ስለ አድዋ፡፡ ዘንድሮ አድዋን በእልህና በቀዝቃዛ የጦርነት ትንቅንቅ በያለንበት ዘራፌዋን በልባችን ጎዝጉዘን አክብረነዋል፡፡ መታሰቢያ የአድዋዊያን አናብስትና አናብርት አሻራዎች ሁሉ በውጋ ፍለጋ ተፈትሸዋል፡፡ የኔ ትውልድ ራሱን መፈለግ የጀመረበት የማንቂያ ደወል የነረተበት 121ኛው አድዋ፡፡ ዝም ብየ ዘው አልሁ አይደል፡፡ እንዴት ናችሁ ኢትየዮጵያውያን? ከነ አንዱ ትንሳኤ ተለይቸ እናንተ ትደጋግሙታላችሁ፡፡ እንኳን አደረሳችሁ ለዳግሚያ ትንሳኤው፡፡ ተመለስሁ:- ታዲያ የዚያን ሰሞን እኔም በፊት ገፄ ላይ ሞቅ ሞቅ ደመቅመቅ አድርጌ አክብሬዋለሁ፡፡ ታዲያ በ120ኛው የአድዋ ድል ቀን ሰሞን አንድ የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበረ ስለ አድዋ ፖን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ጥንስስ ሃሳብ በቴሌቪዥን ቀርበው ከጆሮ የሚደርስ ነገር አብስረውን ሙሉ አንድ አመት ግን የወሬው ደብዛ መጥፋቱን እና የዜና ፍጆታ ሆኖ ቀረ ማለት ነው ብዬ ሃሜተኛ ሆኜ ነበር፡፡ አትፍረዱ ጉጉቴ ቢበረታ እና የአላማው መሳካት አጋር ለመሆን በመፍቀዴ ነው፡፡ ታዲያ ዛሬ ለጉዳዩ የመመካከሪያ ሸንጎ ለመጣል ከተሰናዳ መድረክ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት “የያዘ ሸራ ተሰቅሏል፡፡ ታዲያ እንግሊዘኛው ከአማርኛው ቀድሞ የተፃፈ ቢሆንም ያልተገዛ ኢትዮ...

ጎጃም ልጃገረዶች የእንግጫ ነቀላና ከሰይ አጨዳ

  በግርማው አሸብር እ ንግጫ ነቀላ መልከ ብዙ ሆነ ማህበራዊ ሚና እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ያሉት  በጎጃም ማህበረሰብ ዘንድ ተወደደ በዓል ነው፡፡ አዲስ አመት ሲቃረብ ሰደጥ ሲሆን መስኩ፣ አረንጓዴ ሲለብስ ሜዳው፣ ተራራዎች በአበባ ሲያሸበርቁ ተስፋ የሚለመልምበት ፣ ወገን ከወገን ተነፋፍቆ የሚገናኝበት የደስታ ብርሃን የሚፈካበት ወቅት ምልክት ነው እንግጫ ነቀላ፡፡ ልጃገረዶች ከተፈጥሮ ጋር የሚገናኙበት፣ በተፈጥሮ ገጸ በረከት የሚፈነድቁበት ያም ሆኖ ከአበባው፣ ከሶሪት ላባው፣ በአደይ ሽታና መዓዛው ሁሉ ታድለው በእንግጫ በዓል ዜማ የሚጫወቱበት ሸጋ ወቅት ነው፡፡ በ ጎጃም ልጃገረዶች የእንግጫ ነቀላና ከሰይ አጨዳ በሚል ስያሜ የሚታወቀው የልጃገረዶች ጨዋታ የሚከበረው ነሐሴ ወር በተለይም የቡሄ ሰሞን ነው። ይህ ባህላዊ ጨዋታ የማህበረሰቡ ትውፊት ማንጸባረቂያ ሃይማኖታዊ እሴት ያለው ሲሆን በየአመቱ በመላው ጎጃም አካባቢዎች ይከበራል።በእንግጫ የሣር ዓይነት ነው፡፡ ለምልሞ አገፍግፎ የሚታይ አዲስ ሳር ነው፡፡ በ አዲስ ዓመት ዋዜማ ልጃገረዶች መስክ ወርደው የሚነቅሉት የዕንቁጣጣሽ ብሥራት ነጋሪ ነው፡፡ መስከረም አንድ ቀን ያለው ልዩ ነገር የዘመኑን መለወጥ አስመልክቶ የባሕረ ሐሳብ አዋጁ ይነገራል፡፡ በዓመቱ ውስጥ በዓል የሚውልበት፣ ጾም የሚገባባትን ቀን መምህራኑ እያሰሉ ይናገሩታል፡፡ ዓመቱን በፀሐይና በጨረቃ፣ በዓመተ ዓለም ለምዕመናኑ ይገልጹታል፡፡ ራስ ላይ የታሰረው ደግሞ ለመስቀል በዓል ተቀምጦ ይቆይና ደመራው ላይ ታስሮ ቆይቶ እንዲቃጠል ይደረጋል፡፡ ለራስ ምታትና ለጤንነት ሲባል በማኅበረሰቡ የሚከወን ነው፡፡ የእንግጫ ነቀላ በአል በጎጃም ከሚከበሩ የማይዳሰሱ ባህላዊ ሀብቶቻችን መካከል አንዱ ሲሆን በአሉ የሚከበረዉም የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በ...
 https://girmawashebirblog.wordpress.com/page/2/