Posts

Image
  ማንን እናስታውስ ? Girmaw Ashebir ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ሲታወሱ….!!! * ….. ባለቅኔ፣ መምህር ፣ ጸሐፌ   ተውኔት ፣ ዲፕሎማት፣ አርበኛ፣ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ መዝሙር ግጥም ደራሲ የነበሩት ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ሰኔ 30 ቀን 1939 ዓ . ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በማግስቱም ቀብራቸው በቅዱስ በዓለወልድ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ። የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ አጽም በልማት ምክንያት ከተቀበረበት ቦታ ተነስቶ በትንሽ ሳጥን ተቀምጦ ለሰባት ዓመታት ከቆይ በኋላ ሐምሌ 1 ቀን 2009 ዓ . ም ወደ ትውልድ ቦታቸው ተወሰዶ አጽማቸው ዳግም በደብረ ገነት ኤልያስ ቤተክርስቲያን እንዲያርፍ ተደርጓል። ይህም ማለት ከሞቱ ከሰባ ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው። *** የአማርኛን ስነ ጽሁፍ ካሳደጉት ታላላቅ ኢትዮጵያዊያን መካከል ባለቅኔው ዮፍታሄ ንጉሴ ይጠቀሳሉ፡፡ ዮፍታሄ ንጉሴ የተወለዱት በጎጃም ክፍለ ሀገር በደብረ ኤልያስ በ 1885 ዓ . ም ሲሆን በደብረ ኤልያስ ደብር የጥንቱን የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ትምህርት በሚገባ ተምረዋል፡፡ ደብረ ኤልያስ ደብር የ ” ፍቅር እስከ መቃብር ” ደራሲ ሃዲስ አለማየው የተማሩበት ደብር ነው፡፡ ለዛሬ ከተለያዮ ምንጮች ያገኘናቸውን የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ ስራወች ልናስነብባችሁ ወደናል። … የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ግጥሞች ትንቢታዊ ሲሆኑ በአንድ ስንኝ የሚጽፉት ግጥም ተሰጦአቸው የላቀ መሆኑን ያሳየናል። ለአ...