ማንን እናስታውስ?
Girmaw Ashebir
ቀኝ
ጌታ
ዮፍታሔ
ንጉሴ
ሲታወሱ….!!!
* …..ባለቅኔ፣ መምህር ፣ ጸሐፌ ተውኔት ፣ ዲፕሎማት፣ አርበኛ፣ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ መዝሙር ግጥም ደራሲ የነበሩት ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ሰኔ 30 ቀን 1939 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በማግስቱም ቀብራቸው በቅዱስ በዓለወልድ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ።
የቀኝ ጌታ
ዮፍታሔ
ንጉሴ
አጽም
በልማት
ምክንያት
ከተቀበረበት
ቦታ
ተነስቶ
በትንሽ
ሳጥን
ተቀምጦ
ለሰባት
ዓመታት
ከቆይ
በኋላ
ሐምሌ
1 ቀን
2009 ዓ.ም
ወደ
ትውልድ
ቦታቸው
ተወሰዶ
አጽማቸው
ዳግም
በደብረ
ገነት
ኤልያስ
ቤተክርስቲያን
እንዲያርፍ
ተደርጓል።
ይህም
ማለት
ከሞቱ
ከሰባ
ዓመታት
በኋላ
መሆኑ
ነው።
***
የአማርኛን ስነ
ጽሁፍ
ካሳደጉት
ታላላቅ
ኢትዮጵያዊያን
መካከል
ባለቅኔው
ዮፍታሄ
ንጉሴ
ይጠቀሳሉ፡፡
ዮፍታሄ
ንጉሴ
የተወለዱት
በጎጃም
ክፍለ
ሀገር
በደብረ
ኤልያስ
በ1885
ዓ.ም
ሲሆን
በደብረ
ኤልያስ
ደብር
የጥንቱን
የኢትዮጵያ
ቤተክርስትያን
ትምህርት
በሚገባ
ተምረዋል፡፡
ደብረ
ኤልያስ
ደብር
የ”ፍቅር
እስከ
መቃብር”
ደራሲ
ሃዲስ
አለማየው
የተማሩበት
ደብር
ነው፡፡
ለዛሬ ከተለያዮ
ምንጮች
ያገኘናቸውን
የቀኝ
ጌታ
ዮፍታሄ
ንጉሴ
ስራወች
ልናስነብባችሁ
ወደናል።
…
የቀኝ ጌታ
ዮፍታሄ
ግጥሞች
ትንቢታዊ
ሲሆኑ
በአንድ
ስንኝ
የሚጽፉት
ግጥም
ተሰጦአቸው
የላቀ
መሆኑን
ያሳየናል።
ለአብነት
ያክል
የሚከተሉትም
ምጡቅ
ስንኞቻቸውን
እንመልከት፤
…
የሰማይ አሞራ
ልጠይቅሽ
ወሬ፣
ተቃጥሏል መሰለኝ
ሸተተኝ
አገሬ፡፡
…
ማሽላና ስንዴ
በአንድ
አብረን
ስንቆላ፤
እያረረ ሳቀ
የባህር
ማሽላ፡፡
ከሰል የሚሆኑ
ብዙ
እንጨቶች
ሳሉ፤
ዝግባ ለምን
ይሆን
ይቆረጥ
የሚሉ፡፡
…
“ሰውን
ሰው
ቢወደው
አይሆንም
እንደራስ፣
ታመህ ሳልጠይቅህ
መቅረቴን
አትውቀስ፣
ባውቀው ነው
የመጣሁ
እንደማልመለስ፣
ይማርህ መሀሪው
እስመጣ
ድረስ።
…
በጣሊያን ወረራ
ወቅት
ለፋሺስት
ያገለገሉ
ባንዳዎችን
በማስመልከት
የገጠሙት
ምፀታዊ
ግጥም
እንዲህ
ይላል፡-
“ለጌሾ
ወቀጣ
ማንም
ሰው
አልመጣ
ለመጠጡ ጊዜ
ከየጐሬው
ወጣ፡፡”
…
ሌላኛው የቀኝ
ጌታ
እምቅ
ቅኔ
ደግሞ
“አጥንቱን
ልልቀመው”
የሚለው
ግጥም
ሲሆን
አርበኞቹን
የዶጋሊውን
አሉላ
አባ
ነጋ
እና
ራስ
ጎበናን
በማነፃፀር
የገጠሙት
ግጥም
ነው፤
…
አጥንቱን ልልቀመው
መቃብር
ቆፍሬ፣
ጎበናናን ከሽዋ
አሉላን
ተትግሬ፣
ስመኝ አድሬያለሁ
ትላንትና
ዛሬ፣
አሉላን ለጥይት
ጎበናን
ለጭሬ፣
ጎበና ሴት
ልጁን
ሊያስተምር
ፈረስ፣
አሉላ ሴት
ልጁን
ጥይት
ሲያስተኩስ፣
ሀገሬ ተባብራ
ካልረገጠች
እርካብ፣
ነገራችን ሁሉ
የዕምቧይ
ካብ፣
የዕምቧይ
ካብ።”
ይላል።
…
ቀኝ ጌታ ድንግል
ሀገሬ
ሆይ
የተሰኘውን
ድርሰት
የፃፉት
በስደት
ኢሊባቡር
ሆነው
በ1929
ዓ.ም
ነበር፡፡
ይሄ
ግጥም
ዮፍታሄ
ንጉሴ
ህዝቡ
በፋሺስት
ወረራ
የደረሰበትን
ስደት
የገለፁበት
ስንኝ
ነው፡፡
ቅድስት
ድንግል
ማርያም
ከእስራኤል
ወደ
ግብጽ
ያደረገችውን
ስደት
እና
በኤሮድስ
ህፃናት
መቀላታቸውን
ከኢትዮጵያ
ስደት
ጋር
ያነፃፀሩበት
ግጥምም
ደሞ
እንዲህ
ይነበባል።
…
“ጥንተ
ተደንግሎ
ጥንተ
ተደንግሎ
ህፃናቱ ታርደው
ያንቺም
ልብ
ቆስሎ
ልጅሽ ተሰደደ
አንቺን
ተከትሎ
የህፃናቱ ደም
አዘክሪ
ኩሎ፡፡
አዝማች፤ አስጨነቀኝ
ስደትሽ
እመቤቴ ተመለሺ
እመቤቴ
ተመለሺ።”
***እኒህ ታላቅ ደራሲ በርካታ ድርሰቶችን የጻፉ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ሥራዎቻቸው ለኅትመት አልበቁም።
የሰማይ አ ሞ ራ ልጠይቅሽ ወሬ
ተቃጥሏል መሰለኝ ሸተተኝ አገሬ
~~~~~~~~~~~~~~~
ዕውቁ ባለቅኔ፣ደራሲ፣መምህርና
አርበኛ
ቀኝ
ጌታ
ዮፍታሔ
ንጉሴ
ኢትዮጵያን
ከልጅነቱ
ጀምሮ
ያገለገለ
የሃገር
አድባር
ነው።
ይኼ
የዘመናዊ
ኪነ
ጥበብ
አባት
ቅኔ
እንደዥረት
የሚፈስባት
ጎጃም፣ደብረ
ኤልያስ
ያበቀለችው
የኢትዮጵያ
ልጅ
ገና
በለጋ
ዕድሜው
ባሳዬው
የቅኔ
ችሎታ
እና
የጥበብ
ተሰጥኦ
የቀኝ
ጌትነት
ማዕረግ
ተሰጥቶታል።
በኋላም
በዳግማዉ
ምኒልክ
ትምህርት
ቤት
የግዕዝ፣የአማርኛ
እና
የግብረ
ገብነት
አስተማሪ
በመሆን
ሃገሩን
አገልግሏል።
በጣሊያን ወረራ
ወቅት
ከባድ
የአርበኝነት
ተጋድሎ
አድርጓል።
አፄ
ኃይለ
ሥላሴ
ወደ
ውጪ
ከተሰደዱ
በኋላ
የጣሊያን
ወራሪዎች
ቀኝ
ጌታ
ዮፍታሔን
ከፍተኛ
ክትትል
ያደርጉበት
ስለነበረ
ወደ
ሱዳን
ሃገር
ተሰዶ
ብዙ
የመከራ
ሕይወትን
ገፍቷል።
ከስደት መልስ
የሕግ
መወሰኛ
ምክር
ቤት
ምክትል
ፕሬዝዳንት
በመሆን
ሃገሩን
በቅንነት
ያገለገለው
ቀኝ
ጌታ
ዮፍታሔ
በሕይወት
ዘመኑ
በርካታ
ቲያትሮችን
ፅፏል።
በሀገራችን የመጀመሪያውን
ብሔራዊ
መዝሙር
(ኢትዮጵያ
ሆይ
ደስ
ይበልሽ
ይሰኛል)
የፃፈው
ይኼው
ታላቅ
ሰው
ነው።
በ
1939 ዓ/ም
በተወለደ
52 ዓመቱ
ሕይወቱ
አልፎ
በበዓለ
ወልድ
ቤተክርስቲያን
ሥርዓተ
ቀብሩ
ተፈፅመ።
ከብዙ
ዓመታት
በኋላ(
2001 ዓ/ም)
ቤተ
ክርስቲያኗ
"ቦታውን
ላለማው
ነውና
አፅማችሁን
አንሱልኝ"
የሚል
ማስታወቂያ
አስነገረች።
በዚህ
ጊዜ
ምስጋና
ይግባቸውና
እነ
አቶ
ጀማነህ
ወርቁ
እና
ሌሎቹም
በጎ
ሰዎች
የቀኝጌታን
አፅም
በክብር
አስወጥተው
እዚያው
ቤተ
ክርስቲያን
አንድ
ጠባብ
ክፍል
ውስጥ
በአደራ
አስቀመጡት።
በኋላ ጎጃም፣
ደብረ
ኤልያስ
" አፅሙን
ተቀብዬ
በክብር
እቀብራለሁ"
በማለቷ
ይኼንን
የሚያስተባብር
ኮሚቴ
ተቋቋመ።
ጉዳዩ
የሚዲያ
የሽፋን
እንዲሰጠው
በሚል
የአማራ
በቴሌቪዥን
ደብዳቤ
ተፃፈለት።
በወቅቱም
የአማራ
ቴሌቪዥን
ጋዜጠኞች
አፅሙን
ከመቀበል
ጀምሮ
በክብር
እስከሚያርፍ
ድረስ
የሦስት
ቀን
ቆይታ
አድርገዋል።
በቀን 29 2009 ዓ/ም
የጎጃም
ሕዝብ
በነቂስ
ወጥቶ
የቀኝጌታን
አፅም
ደጀን
ከተማ
ድረስ
በመኼድ
አቀባበል
አደረገ።
በዚያው
ዕለት
ምሽት
አፅሙ
በደብረ
ማርቆስ
ከተማ
ቅዱስ
ማርቆስ
ቤተ
ክርስቲያን
እንዲያርፍ
ተደረርጎ
ስርዓተ
ፆሎት
እና
ፍታት
ተካኼደ።
በመጨረሻም
ሐምሌ
1 ቀን
2009 ዓ/ም
የቀኝ
ጌታ
ዮፍታሔ
የትውልድ
ቀዬ
በሆነችው
ደብረ
ኤልያስ
ቅዱስ
ኤልያስ
ቤተክርስቲያን
አያልነህ
ሙላቱን
ጨምሮ
ብዙ
የኪነ
ጥበብ
ሰዎች
ባሉበት
ድጋሜ
የቀብር
ሥነ
ስርዓቱ
ተካኼደ።
በእኛ
ላይ
ያልሆነ
የለም።
በወቅቱ እነ
አቶ
ተመስገን
ጥሩነህ
ባሉበት
የቀኝ
ጌታ
ዮፍታሔ
ንጉሴን
ሐውልት
ለመገንባት
የመሰረት
ድንጋይ
ተቀመጠ።
የመሰረት
ድንጋይው
አሁንም
ባለበት
ሲሆን
አቶ
ተመስገን
ግን
ወደ
ፌደራል
ተዛውረዋል።
ማለቴ
ሐውልቱ
አልተሰራም
ለማለት
ነው።
"ለምን?"
የሚል
አይጠፋም
መቼስ!።
ባሻዬ!
ብዙ
ጥያቄዎችህ
መልስ
እስኪያገኙ
ድርስ
" ለምን?"
ብለኽ
ጠይቅ።
መውጫ:-
የሰማይ አሞራ
ልጠይቅሽ
ወሬ፥
ተቃጥሏል መሰለኝ
ሸተተኝ
አገሬ።
( ቀኝ
ጌታ
ዮፍታሔ
ንጉሴ)
ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ
ማሽላና
ስንዴ በአንድ አብረን ስንቆላ፤
እያረረ ሳቀ የባህር ማሽላ፡፡
ከሰል የሚሆኑ ብዙ እንጨቶች ሳሉ፤
ዝግባ ለምን ይሆን ይቆረጥ የሚሉ፡፡
የሰማይ አሞራ ልጠይቅሽ ወሬ፣
ተቃጥሏል መሰለኝ ሸተተኝ አገሬ፡፡
ለጌሾ ወቀጣ ማንም ሰው አልመጣ
ለመጠጡ ጊዜ ከየጐሬው ወጣ፡፡
ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ከተውኔት ድርሰታቸው በተጨማሪ መዝሙሮችንና ግጥሞችን ደርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ አንድነትና የህብረት መዝሙር የሚገልጽልንን የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር (ተፈሪ ማርሽ)፣ ወላድ ኢትዮጵያ፣ አጥንቱን ልልቀመው፣ ድንግል አገሬ ሆይ የሚባሉ መዝሙሮችን ደርሰዋል፡፡ አጥንቱን ልልቀመው የሚለው ግጥም አርበኞቹን የዶጋሊውን አሉላ አባ ነጋ እና ራስ ጎበናን በማነፃፀር የገጠሙት ግጥም ሲሆን ድንግል ሀገሬ ሆይ የተሰኘውን ድርሰት የፃፉት በስደት ኢሊባቡር ሆነው በ1929 ዓ.ም ነበር፡፡ ይህ መዝሙር ከመጀመሪያ ረድፍ ከሚጠቀሱት ስራዎቻቸው ቀዳሚው ነው፡፡
ድንግል ሀገሩ ሆይ ጥንተ ተደንግሎ
ጥንተ ተደንግሎ ጥንተ ተደንግሎ
ህፃናቱ ታርደው ያንቺም ልብ ቆስሎ
ልጅሽ ተሰደደ አንቺን ተከትሎ
የህፃናቱ ደም አዘክሪ ኩሎ፡፡
አዝማች፤ አስጨነቀኝ ስደትሽ
እመቤቴ ተመለሺ እመቤቴ ተመለሺ
ይሄ ግጥም ዮፍታሄ ንጉሴ ህዝቡ በፋሺስት ወረራ የደረሰበትን ስደት የገለፁበት ስንኝ ነው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ከእስራኤል ወደ ግብጽ ያደረገችውን ስደት እና በኤሮድስ ህፃናት መቀላታቸውን ከኢትዮጵያ ስደት ጋር ያነፃፀሩበት ግጥምም ነው፡፡ የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ግጥሞች ትንቢታዊ ሲሆኑ በአንድ ስንኝ የሚጽፉት ግጥም ተሰጦአቸው የላቀ መሆኑን ያሳየናል፡
የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ አፃፃፍ ለተከታዮቹ ደራሲያን ምሳሌ ስለነበር አንጋፋነታቸው ታላቅ ዋጋ የሚሰጠው ነው፡፡ ዮፍታሄ በግእዝ ቅኔ የበሰሉ ስለነበሩ አማርኛ የስነ ጽሑፍ ቋንቋ እንዲሆንና እንዲያድግ የላቀ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡
የአማርኛ ስነ ጽሑፍን ለማሳደግ በተውኔት፣ በግጥም፣ በዘፈን እና በመዝሙር ባደረጉት ጥረት በኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ የክብር ቦታ አላቸው፡፡ ባለ ቅኔው ዮፍታሄ ከጣሊያን ወረራ በኋላ እስከ 1941 ዓ.ም የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲሰሩ ቆይተው በ1942 ዓ.ም አርፈዋል፡፡ የባለ ቅኔው ዮፍታሄ ስራዎች ግን ተጽእኖ ፈጥረው ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሸጋገራሉ፡፡
የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ ሥራዎች:--
1. እኔ አይኔን ሰው አማረው (ግጥምና ቅኔ)
2. ዐጥንቱን ልልቀመው፥ መቃብር ቆፍሬ (ግጥምና ቅኔ)
3. ወላድ ኢትዮጵያ ለልጆቿ ብላ (ግጥምና ቅኔ)
4. ጎበዛዝቴ ሆይ ወይ ቆነጃጅቴ (ግጥምና ቅኔ)
5. ሰውን ሰው ቢወደው አይኾንም እንደራስ (ግጥምና ቅኔ)
6. አወይ ጥርሴ ሞኙ ዘወትር ይሥቃል (ግጥምና ቅኔ)
7. ሙናዬ (ግጥምና ቅኔ)
8. የኛማ ሙሽራ (ግጥምና ቅኔ)
9. አንተ ባለጐዛ (ግጥምና ቅኔ)
10. ድንግል አገሬ ሆይ ጥንተ ተደንግሎ (ግጥምና ቅኔ)
11. የእኛማ ሀገር (ግጥምና ቅኔ)
12. ሰለኢትዮጵያ (ግጥምና ቅኔ)
13. ትንሽ ዐማርኛ (ግጥምና ቅኔ)
14. የሥነ- በዓል መዝሙር...እንደመፋቂያ (ግጥምና ቅኔ)
15. ጉሰማዬ (ግጥምና ቅኔ)
16. ተነሱ ታጠቁ (ግጥምና ቅኔ)
17. አብሪ ብርሃንሽን (ግጥምና ቅኔ)
18. የባሕር ዳር ጨፌ (ግጥምና ቅኔ)
19. ባገር ገዳይ፥ቋጥኝ ድንጋይ... (ግጥምና ቅኔ)
20. በለስ ለመለመች (ግጥምና ቅኔ)
21. እስክትመጣ ድረስ... (ግጥምና ቅኔ)
22. ጎሐ ጽባሕ (ግጥምና ቅኔ)
23. አገሬ ኢትዮጵያ...ሞኝ ነሽ ተላላ... (ግጥምና ቅኔ)
24. የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር (ግጥምና ቅኔ)
25. የሰንደቅ ዓላማ መዝሙር ደሙን:ያፈሰሰ፥ተጣማጅ: አርበኛ (ግጥምና ቅኔ)
26. አፋጀሽኝ (ተውኔት)
27. እያዩ ማዘን (ተውኔት)
28. ስለአያ ከምሱና ስለአያ እነባንት ይቀጡ (ተውኔት)
29. እለቄጥሩ /ጎበዝ አየን / (ተውኔት)
30. ጥቅም ያለበት ጨዋታ (ተውኔት)
31. የሕዝብ ፀፀት፥የእመት በልዩ ጉዳት (ተውኔት)
32. የሆድ አምላኩ ቅጣት (ተውኔት)
33. ዕርበተ ፀሐይ (ተውኔት)
34. ምስክር (ተውኔት)
35. ያማረ ምላሽ (ተውኔት)
36. ዳዲቱራ (ተውኔት)
37. ሞሽሪት ሙሽራ (ተውኔት)
38. መሸ በከንቱ፥ ሥራ ለፈቱ (ተውኔት)
39. ጠረፍ ይጠበቅ (ተውኔት)
40. ዓለም አታላይ (ተውኔት)
41. የደንቆሮዎች ትያትር (ተውኔት)
42. ንጉሡና ዘውድ (ተውኔት)

Comments
Post a Comment